በማግስቱም ጧት በለዓም ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፣ “ዐብሬአችሁ እንዳልሄድ እግዚአብሔር ከልክሎኛልና እናንተ ወደ አገራችሁ ተመለሱ አላቸው።”
ዘኍል 22:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሞዓብ አለቆች ወደ ባላቅ ተመልሰው፣ “በለዓም ዐብሮን ለመምጣት እንቢ አለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞዓብ ሹማምንት ተነሡ፥ ወደ ባላቅም ሄደው፦ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት ፍቃደኛ አልሆነም” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሞአብ ሹማምንት ወደ ባላቅ ተመለሱና በለዓም አብሮአቸው ለመምጣት እምቢ እንዳለ ነገሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞዓብ አለቆችም ተነሡ፤ ወደ ባላቅም መጥተው፥ “በለዓም ከእኛ ጋር ይመጣ ዘንድ አልፈቀደም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞዓብ አለቆች ተነሡ፥ ወደ ባላቅም መጥተው፦ በለዓም ከእኛ ጋር ይመጣ ዘንድ አልፈቀደም አሉት። |
በማግስቱም ጧት በለዓም ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፣ “ዐብሬአችሁ እንዳልሄድ እግዚአብሔር ከልክሎኛልና እናንተ ወደ አገራችሁ ተመለሱ አላቸው።”