ዘኍል 21:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እሳት ከሐሴቦን ወጣ፤ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ተንቦገቦገ፤ የሞዓብን ዔር፣ በአርኖን ከፍታዎች የሚኖሩትንም አለቆች በላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ የሞዓብን ዔር፥ የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሐሴቦን እሳት ወጣ፤ ነበልባልም ከሲሖን ከተማ፥ የሞአብን ዔር አጠፋ የአርኖንንም ከፍተኛ ቦታዎች ደመሰሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ እስከ ሞዓብ ድረስ በላ፤ የአርኖን ሐውልቶችንም ዋጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ የሞዓብን ዔር፥ የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ፤ |
ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል።
የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣ በሞዓብ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መኻል፣ በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።
ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሞዓባውያን ምድር አንዳችም መሬት ስለማልሰጣችሁ አታስቸግሯቸው፤ ለጦርነትም አታነሣሧቸው፤ ዔርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ” አለኝ።
“የእሾኽ ቍጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾኽ ቍጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ!’ አላቸው።
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ትውጣና እናንተን፣ የሴኬምንና የቤት ሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፣ ከሴኬምና ከቤት ሚሎን ገዦች ትውጣና አቢሜሌክን ትብላ።”