እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
ዘኍል 18:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍርባናችሁም ከዐውድማ እንደ ገባ እህል ወይም ከመጭመቂያ እንደ ወጣ ወይን ሆኖ ይቈጠርላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ስጦታ የምታቀርቡት ቁርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ሙላት ይቈጠርላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ልዩ መባ አንድ ገበሬ ከአዲስ እህል ወይም የወይን ጠጅ ዐሥራት አውጥቶ እንደሚሰጠው ዐይነት ሆኖ ይቈጠርላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባችሁም እንደ እህል ዐውድማው ስንዴና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማንሣት ቍርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል። |
እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
“ሌዋውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ርስት አድርጌ የምሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እናንተም ካገኛችሁት ላይ አንድ ዐሥረኛ በማውጣት ለእግዚአብሔር መባ አድጋችሁ ታቀርባላችሁ።
እናንተም ከእስራኤላውያን ላይ ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ በዚሁ ዐይነት ለእግዚአብሔር መባ ታቀርባላችሁ፤ ከዚሁም የእግዚአብሔር ድርሻ የሆነውን ዐሥራት ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።
“ሌዋውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ምርጥ የሆነውን ክፍል በምታቀርቡበት ጊዜ፣ እንደ ዐውድማ ምርት ወይም እንደ ወይን መጭመቂያ ውጤት ሆኖ ይቈጠርላችኋል።