ዘኍል 18:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የተሰጠ በእስራኤል ያለ ማንኛውም ነገር ሁሉ የአንተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ዘንድ እርም የሆነው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእስራኤል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለእኔ የተለየ ነገር ሁሉ ለእናንተ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተከለከለው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ዘንድ እርም የሆነው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። ከሰው ወይም ከእንስሳ ቢሆን፥ |
“ ‘ነገር ግን ለእግዚአብሔር የተሰጠ፣ ማንኛውም ነገር ሰውም ሆነ እንስሳ ወይም በውርስ የተገኘ መሬት አይሸጥም፤ አይዋጅምም። ለእግዚአብሔር የተሰጠ ማንኛውም ነገር እጅግ የተቀደሰ ነውና።