እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአሮን በትር ለዐመፀኞቹ ምልክት እንድትሆን መልሰህ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራት፤ እነርሱ እንዳይሞቱም በእኔ ላይ የሚያደርጉትን ማጕረምረም ይህ ይገታዋል” አለው።
ዘኍል 17:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ በትሮቹን ከእግዚአብሔር ፊት አውጥቶ ወደ እስራኤላውያን ሁሉ አመጣቸው፤ እነርሱም አዩ፤ እያንዳንዱም ሰው የየራሱን በትር ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከጌታ ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፥ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም በትሮቹን ሁሉ አምጥቶ ለእስራኤላውያን አሳያቸው፤ የሆነውን ሁሉ ከተመለከቱ በኋላ እያንዳንዱ መሪ የራሱን በትር ወሰደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በትሮቹን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፤ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፥ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። |
እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአሮን በትር ለዐመፀኞቹ ምልክት እንድትሆን መልሰህ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራት፤ እነርሱ እንዳይሞቱም በእኔ ላይ የሚያደርጉትን ማጕረምረም ይህ ይገታዋል” አለው።
በማግስቱም ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ በሌዊ ቤት ስም የቀረበችው የአሮን በትር ማቈጥቈጥ ብቻ ሳይሆን እንቡጥ አውጥታ፣ አብባና አልሙን አፍርታ አገኛት።