La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 15:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ትእዛዞቼን ሁሉ ለመፈጸም ታስባላችሁ፤ ለአምላካችሁም የተቀደሳችሁ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ትእዛዜን ሁሉ አስታውሱት አድርጉትም፥ ለአምላካችሁም ቅዱሳን ሁኑ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በልብሶቻችሁም ጫፍ ላይ የሚታዩት ዘርፎች ትእዛዞቼን ሁሉ እንድትፈጽሙ ያስታውሱአችኋል፤ እናንተም በፍጹም ለእኔ የተገዛችሁ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ትእ​ዛ​ዙን ታስ​ቡና ታደ​ርጉ ዘንድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ቅዱ​ሳን ትሆኑ ዘንድ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ትእዛዜን ሁሉ ታስቡና ታደርጉ ዘንድ፥ ለአምላካችሁም ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ ዘርፉ በልብሳችሁ ላይ እንዲታይ ይሁን።

Ver Capítulo



ዘኍል 15:40
10 Referencias Cruzadas  

ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጕት ላይ ይሆናል።


“ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ጉባኤ እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።


“ትእዛዞቼን ጠብቁ፤ አድርጓቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው።


በፊቱ ቅዱስና እንከን አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣


በቈላስይስ ለሚኖሩ፣ በክርስቶስ ለሆኑ ቅዱሳንና ታማኝ ወንድሞች፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


እግዚአብሔር በቅድስና እንድንመላለስ እንጂ ለርኩሰት አልጠራንምና።