ዘኍል 15:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባዘጋጃችሁት ቍጥር ልክ ይህን ለእያንዳንዱ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳዘጋጃችሁት ቍጥር መጠን፥ እንዲሁ እንደ ቁጥራቸው ለእያንዳንዱ ታደርጋላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንድ እንስሳ በላይ በሚቀርብበት ጊዜ አብሮት የሚቀርበውም የእህል ቊርባን በተመሳሳይ ሁኔታ ይጨምራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዳዘጋጃችሁት ቍጥር፥ እንዲሁ እንደ ቍጥራቸው ለእያንዳንዱ ታደርጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳዘጋጃችሁት ቍጥር፥ እንዲሁ እንደ ቍጥራቸው ለእያንዳንዱ ታደርጋላችሁ። |
“ ‘ማንኛውም የአገር ተወላጅ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች በዚሁ ሁኔታ ያድርግ።