ዘኍል 10:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባረፉ ጊዜም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በብዙ ሺሕ ወደሚቈጠሩት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባረፈም ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤል ልጆች ተመለስ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃል ኪዳኑም ታቦት ጒዞውን ባቆመ ጊዜ “በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤላውያን ሕዝብ ተመለስ” ይል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰፈራቸውም በተጓዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀን ቀን በላያቸው ላይ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባረፈም ጊዜ፦ አቤቱ፥ ወደ እስራኤል እልፍ አእላፋት ተመለስ ይል ነበር። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን? ስለ ባሮችህ ስትል፣ ስለ ርስትህ ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።