እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።
ዘኍል 10:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ማደሪያው ተነቀለ፤ ድንኳኑን የተሸከሙት ጌርሶናውያንና ሜራሪያውያንም ጕዞ ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማደሪያውም ተነቀለ፤ ማደሪያውንም የተሸከሙት የጌድሶን ልጆችና የሜራሪ ልጆች ተጓዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ድንኳኑ ተነቅሎ፥ ድንኳኑን የተሸከሙት የጌርሾንና የሜራሪ ጐሣዎች ተጓዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳኑም ተነቀለ፤ ድንኳኑንም የተሸከሙ የጌድሶን ልጆችና የሜራሪ ልጆች ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማደሪያውም ተነቀለ፤ ማደሪያውንም የተሸከሙ የጌድሶን ልጆችና የሜራሪ ልጆች ተጓዙ። |
እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።
ስለዚህ ከቶ የማይናወጥ መንግሥት ስለምንቀበል እግዚአብሔርን እናመስግን፤ ደግሞም ደስ በሚያሠኘው መንገድ በአክብሮትና በፍርሀት እናምልከው፤
ክርስቶስ አሁን ስላሉት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ፣ በሰው እጅ ወዳልተሠራችው፣ ከዚህ ፍጥረት ወዳልሆነችው ታላቅና ፍጹም ድንኳን ገባ።