ነህምያ 9:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ቀድምኤል፣ ሰበንያ፣ ቡኒ፣ ሰራብያ፣ ባኒ፣ ክናኒ፣ በመውጫ ደረጃዎች ላይ ቆሙ፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርም በታላቅ ድምፅ ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌዋውያኑ መድረክ ላይ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ቃድምኤል፥ ሽባንያ፥ ቡኒ፥ ሼሬብያ፥ ባኒ፥ ክናኒ ቆመው ወደ ጌታ አምላካቸው በታላቅ ድምፅ ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሌዋውያኑ መቆሚያ መድረክ ነበር፤ በዚያም ላይ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ቡኒ፥ ሼሬብያ፥ ባኒና ከናኒ በመቆም፥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያኑም ኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ የሰራብያ ልጅ ሴኬንያ፥ የከናኒ ልጆችም በደረጃዎች ላይ ቆመው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር በታላቅ ድምፅ ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያኑም ኢያሱና ባኒ፥ ቀድምኤል፥ ሰበንያ፥ ቡኒ፥ ሰራብያ፥ ባኒ፥ ክናኒ በደረጃዎች ላይ ቆመው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር በታላቅ ድምፅ ጮኹ። |
ከርሱ ቀጥሎ ሌዋውያኑ በባኒ ልጅ በሬሁ ሥር ሆነው የዕድሳት ሥራ ሠሩ። ከርሱ ቀጥሎ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ ሐሸብያ አውራጃውን መልሶ ሠራ።
ጸሓፊው ዕዝራ ለዚሁ ተብሎ በተሠራውና ከፍ ብሎ በሚገኘው የዕንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡም በስተ ቀኙ በኩል መቲትያ፣ ሽማዕ፣ ዓናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ፣ መዕሤያ፣ በስተ ግራው በኩል ደግሞ ፈዳያ፣ ሚሳኤል፣ መልክያ፣ ሐሱም፣ ሐሽበዳና፣ ዘካርያስና ሜሱላም ቆመው ነበር።
ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን፣ ፌልያ ሕዝቡ በዚያው ቆመው እንዳሉ ሕጉን አስረዷቸው።
ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ቀድምኤል፣ ባኒ፣ አሰበንያ፣ ሰራብያ፣ ሆዲያ፣ ሰበንያና ፈታያ፣ “ተነሥታችሁ ቁሙ፤ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የሚኖረውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱ” አሉ። “ክቡር ስምህ የተመሰገነ ይሁን፤ ከምስጋና ሁሉና ከውዳሴም በላይ ከፍ ከፍ ይበል።