ነህምያ 9:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በያሉበትም ቦታ ቆመው ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ሩብ ቀን አነበቡ፤ የቀረውን ሩብ ቀን ደግሞ ንስሓ በመግባትና ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር በመስገድ አሳለፉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 በየስፍራቸውም ቆመው የጌታ አምላካቸውን የሕግ መጽሐፍ የቀኑ ሩብ ያህል አነበቡ፥ የቀኑ ሩብ ደግሞ እየተናዘዙና፥ ለጌታ አምላካቸው እየሰገዱ አሳለፉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እዚያው እንደ ቆሙም፥ የአምላካቸው የእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ሦስት ሰዓት ሙሉ ተነበበላቸው፤ ሌላም ሦስት ሰዓት ኃጢአታቸውን በመናዘዝ፥ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በየስፍራቸውም ቆመው የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን የሕግ መጽሐፍ አነበቡ፤ ለእግዚአብሔርም ተናዘዙ፤ ለአምላካቸውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በየስፍራቸውም ቆመው የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን የሕግ መጽሐፍ የቀን ሩብ ያህል አነበቡ ሦስት የቀን ሩብም ያህል ተናዘዙ፥ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ሰገዱ። Ver Capítulo |