ነህምያ 2:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደ ነበረችና ንጉሡም ምን እንዳለኝ ነገርኋቸው። እነርሱም፣ “እንደ ገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉ በኋላ ይህን መልካም ሥራ ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም የሆነችው የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደሆነችና ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። ለመልካም ሥራ እጃቸውን አበረቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጠል አድርጌም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንና እንዴትም እንደ ረዳኝ፥ ንጉሠ ነገሥቱም የነገረኝን ሁሉ ገለጥሁላቸው። እነርሱም “እንደገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉኝ በኋላ፥ ይህን በጎ ሥራ ለመጀመር ተዘጋጁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። “ተነሡ እንሥራ” አልኋቸው። እጆቻቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ። |
የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።
ከዚህ በኋላም ንጉሡ ጠንክሮ በመሥራት፣ ከቅጥሩ የፈራረሱትን ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ማማ ሠራበት፤ በውጭ በኩልም ሌላ ቅጥር በመገንባት የዳዊትን ከተማ ድጋፍ እርከን አጠናከረ፤ እንደዚሁም ብዙ የጦር መሣሪያዎችንና ጋሻዎችን ሠራ።
እግዚአብሔር ደስ እንዲሰኙ ስላደረጋቸው የቂጣን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አከበሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ልብ ለውጦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ቤት ሥራ እንዲያግዛቸው አድርጎ ነበር።
እንዲሁም ለንጉሡ ደን ጠባቂ ለአሳፍ፣ በቤተ መቅደሱ አጠገብ ላለው ግንብ በሮች፣ ለከተማዪቱ ቅጥርና እኔም ለምገባበት ቤት ሠረገላ የሚሆን ዕንጨት እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይጻፍልኝ፤” መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ ነበረችና ንጉሡም ፈቀደልኝ።