ማቴዎስ 9:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሲወጡ፣ በጋኔን የተያዘ ድዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየወጡ እያለ እነሆ ጋኔን ያደረበትን ዲዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይኖቻቸው የተከፈቱላቸው ሰዎች ወጥተው በሄዱ ጊዜ ሌሎች ሰዎች ጋኔን ያደረበትን አንድ ድዳ ሰው ወደ ኢየሱስ አመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሲወጡ እነሆ ጋኔን ያደረበትን ድዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሲወጡ እነሆ፥ ጋኔን ያደረበትን ዲዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። |
ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ሕዝቡም በተለያዩ በሽታዎች የታመሙትን፣ በክፉ ደዌ የሚሠቃዩትን፣ አጋንንት ያደሩባቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።