ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ “እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳስሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።
ማቴዎስ 9:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ሰዎቹን በማናገር ላይ ሳለ፣ አንድ የምኵራብ አለቃ መጥቶ ከፊቱ ተደፍቶ፣ “ልጄ አሁን ሞተችብኝ፤ በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ሲነግራቸው ሳለ እነሆ አንድ ገዢ መጥቶ እየሰገደ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ይህን ሲነግራቸው ሳለ፥ አንድ የምኲራብ አለቃ ወደ እርሱ መጣ፤ በግንባሩም በኢየሱስ ፊት ተደፍቶ፥ “እነሆ፥ ልጄ አሁን ሞተችብኝ፤ ነገር ግን አንተ መጥተህ እጅህን ብትጭንባት ትድናለች” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ሲነግራቸው አንድ መኰንን መጥቶ “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፤” እያለ ሰገደለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኵኦንን መጥቶ፦ ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች እያለ ሰገደለት። |
ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ “እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳስሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።
አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቍማዳ ማንም አያስቀምጥም፤ ይህ ከሆነ አቍማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቍማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ነገር ግን አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቍማዳ ይጨመራል፤ በዚህ ሁኔታ የወይን ጠጁና አቍማዳው በደኅና ተጠብቀው ይቈያሉ።”
የምኵራቡ አለቃ ግን፣ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ ሕዝቡን፣ “ሥራ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው።
ማርያምም ኢየሱስ ወደ ነበረበት ቦታ ደርሳ እንዳየችው፣ እግሩ ላይ ተደፍታ፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው።