ማቴዎስ 7:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም በዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ ወንድምህን፣ ‘ዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ ማለት እንዴት ትችላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም እነሆ በዓይንህ ምሰሶ እያለ ወንድምህን ‘ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣልህ ፍቀድልኝ’ እንዴት ትለዋለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞስ በአንተ ዐይን ግንድ እያለ፥ ወንድምህን ‘እስቲ በዐይንህ ያለውን ጒድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም ወንድምህን ‘ከዐይንህ ጕድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ’ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዐይንህ ምሰሶ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። |
በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ ወንድምህን፣ ‘ወንድሜ ሆይ፤ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ልትለው ትችላለህ? አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።