7 በሞኝ አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ የሰለለ የሽባ ሰው እግር ነው።
7 በምሳሌ የሚናገር ሞኝ፥ እንደተንጠለጠሉ የአንካሳ እግሮች ነው።
7 ሞኝ በምሳሌ የሚጠቀመው ሽባ ሰው በአንካሳ እግሮቹ የሚጠቀመውን ያኽል ነው።
በሞኞች አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።
መልካም አነጋገር ለሞኝ አይሰምርለትም፤ ለገዥ ሐሰተኛ አንደበት የቱን ያህል የከፋ ይሆን!
በገዛ ምላሳቸው ያሰናክላቸዋል፤ ጥፋትንም ያመጣባቸዋል፤ የሚያዩአቸውም ሁሉ በትዝብት ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።
እርሱም፣ “ ‘ባለመድኀኒት ሆይ፤ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም ስታደርግ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ ከተማ ደግሞ አድርግ’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም” አላቸው።
በሞኝ እጅ መልእክትን መላክ፣ የገዛ እግርን እንደ መቍረጥ ወይም መርዝ እንደ መጋት ነው።
ለሞኝ ክብር መስጠት፣ በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።