ማቴዎስ 6:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት አጥብቀው ይሻሉና፤ የሰማዩ አባታችሁም እነዚህ ሁሉ ለእናንተ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብም እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ለማግኘትማ አሕዛብም ይፈልጋሉ፤ እናንተ ይህ ሁሉ እንደሚያስፈልጋችሁ፥ የሰማይ አባታችሁ ያውቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤ ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ። ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤ ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤ ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ።
ታዲያ፣ ለራስህ ታላቅ ነገር ትሻለህን? በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ጥፋት አመጣለሁና አትፈልገው፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ሁሉ ሕይወትህ እንዲተርፍልህ አደርጋለሁ።’ ”