ማቴዎስ 27:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ሲከስሱት ግን ምንም መልስ አልሰጠም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሊቃነ ካህናትና በሽማግሌዎች ሲከሰስ ምንም አልመለሰም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ሲወነጅሉት ምንም መልስ አልሰጠም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም። |
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም፣ “በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ ንገረን” አለው።
ጃንደረባው ያነብብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም።