ማቴዎስ 26:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱ ይህን በተመለከቱ ጊዜ ተቈጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቆጡና እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱ ይህን አይተው ተቈጡና እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሽቶ ለምን በከንቱ ባከነ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና “ይህ ጥፋት ለምንድር ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቍኦጡና፦ ይህ ጥፋት ለምንድር ነው? |
እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
እንዲህም ትላላችሁ፤ “መስፈሪያውን በማሳነስ፣ ዋጋውን ከፍ በማድረግ፣ በሐሰተኛ ሚዛን በማጭበርበር፣ እህል እንድንሸጥ፣ የወር መባቻ መቼ ያበቃል? ስንዴም ለገበያ እንድናቀርብ፣ ሰንበት መቼ ያልፋል?”
ደግሞም፣ ‘ይህ ድካም ነው’ በማለት በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “በቅሚያ የመጣውን፣ ዐንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ቍርባን አድርጋችሁ ስታቀርቡ ከእጃችሁ መቀበል ይገባኛልን?” ይላል እግዚአብሔር፤
አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ አንድ ብልቃጥ የአልባስጥሮስ ሽቱ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማእድ ላይ ተቀምጦ ሳለም በራሱ ላይ አፈሰሰችው።