ማቴዎስ 26:72 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በመሐላ ቃል፣ “ሰውየውን አላውቀውም!” ሲል ዳግመኛ ካደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰውየውን አላውቀውም” ብሎ እየማለ ካደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስም “ይህን የምትዪውን ሰው አላውቀውም!” ሲል በመማል እንደገና ካደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም ሲምል “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ካደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳግመኛም ሲምል፦ ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ካደ። |
“የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ፣ እናንተ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ወይም በጽድቅ ሳይሆን፣ የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ ይህን ስሙ!
“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ በዚያ ቆመው የነበሩት ሰዎች ቀርበው ጴጥሮስን፣ “አነጋገርህ ስለሚያጋልጥህ፣ በርግጥ አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።