ማቴዎስ 25:45 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜ እርሱም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቼ ለአንዱ አለማድረጋችሁ፣ ለእኔ እንዳላደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያንጊዜ እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ያላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ እንዳላደረጋችሁት ነው።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያላደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳላደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያን ጊዜ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም፤’ ብሎ ይመልስላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል። |
እንደ አንበሳ አድፍጠዋል፤ እንደ እንስቲቱም አንበሳ አድብተዋል፤ ሊቀሰቅሳቸውስ የሚችል ማን ነው? “የሚባርኩህ ቡሩክ፣ የሚረግሙህም ርጉም ይሁኑ።”
“እነርሱም መልሰው፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ተርበህ ወይም ተጠምተህ፣ እንግዳ ሆነህ ወይም ታርዘህ፣ ታምመህ ወይም ታስረህ አይተን መቼ አልደረስንልህም’ ይሉታል።