ማቴዎስ 23:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መምህራችሁ አንዱ ክርስቶስ ስለ ሆነ፣ ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሪዎች ተብላችሁ አትጠሩ፥ መሪአችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊቃችሁ ክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ‘ሊቃውንት’ ተብላችሁ አትጠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና ‘ሊቃውንት’ ተብላችሁ አትጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና፦ ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። |
እርሱም፣ “ወደ ከተማ ሄዳችሁ እገሌ የተባለውን ሰው፣ ‘መምህር ጊዜዬ ተቃርቧልና ከደቀ መዛሙርቴ ጋራ ፋሲካን በቤትህ አከብራለሁ ብሏል’ በሉት” አላቸው።