ማቴዎስ 22:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያም ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘የሰርጉ ድግስ ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን የተጋበዙት የሚገባቸው ሆነው ስላልተገኙ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ባርያዎቹን እንዲህ አላቸው ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ የታደሙት ግን የተገቡ አልሆኑም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘እነሆ፥ የሠርጉ ድግስ ተዘጋጅቶአል፤ የተጠሩት ግን ለግብዣው የተገቡ አልሆኑም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ባሮቹን ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ባሮቹን፦ ሰርጉስ ተዘጋጅቶአል፥ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤ |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ዐብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያም ጊዜ ይጾማሉ።
ጳውሎስና በርናባስም በድፍረት እንዲህ አሏቸው፤ “የእግዚአብሔር ቃል በመጀመሪያ ለእናንተ መነገር አለበት፤ እናንተ ግን ናቃችሁት፤ በዚህም የዘላለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ላይ ስለ ፈረዳችሁ፣ እኛም ወደ አሕዛብ ዞር ለማለት እንገደዳለን።
ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍርድ ቅን መሆኑን የሚያመለክት ነው፤ ከዚህም የተነሣ መከራን ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የበቃችሁ ሆናችሁ ትቈጠራላችሁ።
ነገር ግን ልብሳቸውን ያላሳደፉ ጥቂት ሰዎች በሰርዴስ ከአንተ ጋራ አሉ፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋራ ይሄዳሉ፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።