ማቴዎስ 19:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትህንና እናትህን አክብር፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤ የሚሉት ትእዛዞች ናቸው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባትህንና እናትህንአክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። |
“ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም በመካከልህ ከሚኖር በማንኛውም ሰው ላይ ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ሰውየውም መልሶ፣ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህና በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ’ ይላል” አለው።
“አታመንዝር”፣ “አትግደል”፣ “አትስረቅ”፣ “አትመኝ” የሚሉትና ሌሎችም ትእዛዞች ቢኖሩም፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በዚህ በአንድ ሕግ ተጠቃልለዋል።
አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።