Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 13:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “አታመንዝር”፣ “አትግደል”፣ “አትስረቅ”፣ “አትመኝ” የሚሉትና ሌሎችም ትእዛዞች ቢኖሩም፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በዚህ በአንድ ሕግ ተጠቃልለዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ አትመኝ፤” የሚለው እና ሌላም ትእዛዝ ቢኖር፤ በዚህ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤” በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ የሌላ ሰው የሆነውን ማናቸውንም ነገር አትመኝ” የሚሉት ትእዛዞችና ሌሎችም ትእዛዞች ሁሉ “ሰውን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ” በሚለው በአንዱ ትእዛዝ ተጠቃለው ይገኛሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በኦ​ሪት እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “አታ​መ​ን​ዝር፤ አት​ግ​ደል፤ አት​ስ​ረቅ፤ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር፥ አት​መኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእ​ዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁ​ሉም ራስ “ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 13:9
13 Referencias Cruzadas  

“ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም በመካከልህ ከሚኖር በማንኛውም ሰው ላይ ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ዐብሯችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ገዛ ወገናችሁ ይታይ፤ እንደ ራሳችሁም ውደዱት፤ እናንተም በግብጽ መጻተኞች ነበራችሁና፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤


‘አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ አታታልል፣ አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚለውን ትእዛዝ ታውቃለህ።”


ሁለተኛውም ይህ ነው፤ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።’ ከእነዚህም የሚበልጥ ትእዛዝ የለም።”


ሰውየውም መልሶ፣ “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህና በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ’ ይላል” አለው።


‘አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚለውን ትእዛዝ ታውቃለህ።”


ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤ ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos