ማቴዎስ 10:42 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ በደቀ መዝሙር ስም ብቻ የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋውን አያጣም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ ደቀ መዝሙር በመሆኑ፥ ከነዚህ ታናናሾች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም። |
ስለዚህ በሰገነቱ ላይ አንዲት ትንሽ ክፍል ቤት ሠርተን ዐልጋና ጠረጴዛ፣ ወንበርና ፋኖስ እናስገባለን፤ ከዚያም ወደ እኛ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።”
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣ በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ! እረኛውን ምታ፣ በጎቹም ይበተናሉ፤ እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”
“ከእነዚህ ከታናናሾች መካከል አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ እላችኋለሁና፤ በሰማይ ያሉት መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉ፤ [
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ መልሳችሁ ለመቀበል ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፤ በዚህም ወሮታችሁ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።