ማርቆስ 8:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ይህን በግልጽ ነገራቸው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ወስዶ ይገሥጸው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ይህን በግልጽ ነገራቸው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ወስዶ ይገሥጸው ጀመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ነገር በግልጥ ነገራቸው፤ በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ለብቻው ገለል አድርጎት ይገሥጸው ጀመር። “እንዲህ አትበል” ሲል ተቈጣው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር። |
ኢየሱስ ግን ትራስ ተንተርሶ ከጀልባዋ በስተኋላ በኩል ተኝቶ ነበር። እነርሱም ቀስቅሰውት፣ “መምህር ሆይ፤ ስንጠፋ አይገድድህምን?” አሉት።
ማርታ ግን በሥራ ብዛት ትባክን ነበርና ወደ እርሱ ቀርባ፣ “ጌታ ሆይ፤ እኅቴ ሥራውን ለእኔ ብቻ ጥላ ስትቀመጥ ዝም ትላለህን? እንድታግዘኝ ንገራት እንጂ” አለችው።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ፤ አይሁድ በተሰበሰቡበት ምኵራብ፣ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተምሬአለሁ፤ በስውር የተናገርሁት የለም።