ማርቆስ 7:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም ግሪካዊት፣ በትውልዷም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች። እርሷም ኢየሱስ ጋኔኑን ከልጇ እንዲያስወጣላት ለመነችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትዮዋም ግሪካዊት፥ በትውልዷም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች። እርሷም ኢየሱስ ርኩስ መንፈሱን ከልጇ እንዲያስወጣላት ለመነችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋም ከሲሮፊኒቃውያን ወገን የሆነች ግሪካዊት ነበረች፤ እርስዋ ከልጅዋ ጋኔን እንዲያወጣላት ኢየሱስን ለመነችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው። |
ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ሕዝቡም በተለያዩ በሽታዎች የታመሙትን፣ በክፉ ደዌ የሚሠቃዩትን፣ አጋንንት ያደሩባቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
በዚያ ግሪክ ወይም ይሁዲ፣ የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ፣ አረማዊ ወይም እስኩቴስ፣ ባሪያ ወይም ጌታ ብሎ ልዩነት የለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው።