Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 7:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሴትዮዋም ግሪካዊት፥ በትውልዷም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች። እርሷም ኢየሱስ ርኩስ መንፈሱን ከልጇ እንዲያስወጣላት ለመነችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሴትዮዋም ግሪካዊት፣ በትውልዷም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች። እርሷም ኢየሱስ ጋኔኑን ከልጇ እንዲያስወጣላት ለመነችው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሴትዮዋም ከሲሮፊኒቃውያን ወገን የሆነች ግሪካዊት ነበረች፤ እርስዋ ከልጅዋ ጋኔን እንዲያወጣላት ኢየሱስን ለመነችው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 7:26
7 Referencias Cruzadas  

እነሆ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አገር መጥታ “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ ማረኝ፤ ሴት ልጄ በጋኔን ክፉኛ ተይዛለች” እያለች ጮኸች።


ጎዳኖቼም ከፍ ከፍ ይላሉ። እነሆ፥ እነዚህ ከሩቅ፥ እነሆም፥ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፥ እነዚህም ከሲኒም አገር ይመጣሉ።”


በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።


በክርስቶስ ኢየሱስ ሁላችሁም አንድ ናችሁና አይሁዳዊ ወይም ግሪካዊ የለም፥ ባርያ ወይም ነጻ ሰው የለም፥ ወንድ ወይም ሴት የለም።


ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።


ወዲያው ግን ትንሺቱ ልጇ በርኩስ መንፈስ የተያዘችባት አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ወደቀች።


እርሱ ግን፥ “የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መጣል ተገቢ ስላልሆነ፥ መጀመሪያ ልጆቹ ጠግበው ይብሉ” አላት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios