በተሻገሩም ጊዜ፣ ወደ ጌንሴሬጥ ምድር ደረሱ፤ ጀልባዋንም እዚያው አስጠጉ።
በተሻገሩም ጊዜ፥ ጌንሴሬጥ ደርሰው ወረዱ፤ ጀልባዋንም እዚያው አቆሙ።
ባሕሩን ተሻግረው፥ ወደ ጌንሳሬጥ ደረሱ፤ ጀልባዋን ወደ ምድር አስጠግተው አሰሩ፤
ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ፤ ታንኳይቱንም አስጠጉ።
ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ ታንኳይቱንም አስጠጉ።
ወዲያው ከጀልባዋ እንደ ወረዱም፣ ሕዝቡ ኢየሱስን ዐወቁት፤
ሕዝቡ ዙሪያውን እያጨናነቁት የሚያስተምረውን የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰሙ፣ ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ሐይቅ አጠገብ ቆሞ ነበር፤