የእግዚአብሔርን ስም የሚሳደብ ማንኛውም ሰው ይገደል፤ ማኅበሩ ሁሉ ይውገሩት፤ መጻተኛም ሆነ የአገር ተወላጅ የእግዚአብሔርን ስም ከሰደበ ይገደል።
ማርቆስ 3:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጆች ኀጢአትና የሚሳደቡት ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእውነት እላችኋለሁ፤ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ፥ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእውነት እላችኋለሁ፤ ሰዎች የሚሠሩት ኃጢአትና የሚናገሩት ስድብ ሁሉ ይቅር ይባልላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እውነት እላችኋለሁ፤ ለሰው ልጆች ኀጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ |
የእግዚአብሔርን ስም የሚሳደብ ማንኛውም ሰው ይገደል፤ ማኅበሩ ሁሉ ይውገሩት፤ መጻተኛም ሆነ የአገር ተወላጅ የእግዚአብሔርን ስም ከሰደበ ይገደል።
ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ኀጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይጸልይ፤ እግዚአብሔርም ለሞት የማያበቃ ኀጢአት ላደረጉት ሕይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃም ኀጢአት አለ፤ ስለዚህኛው ግን ይጸልይ አልልም።