ከዚያም ዮሴፍ የአባቱ የእስራኤል ሬሳ እንዳይፈርስ ባለመድኀኒት የሆኑ አገልጋዮቹ በመድኀኒት እንዲቀቡት አዘዘ። ባለመድኀኒቶቹም እንዳይፈርስ ሬሳውን በመድኀኒት ቀቡት።
ማርቆስ 16:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰንበት ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሄደው የኢየሱስን ሥጋ ለመቀባት ሽቱ ገዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰንበት ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፥ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሄደው የኢየሱስን ሥጋ ለመቀባት ሽቱ ገዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰንበት ቀን ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም፥ የያዕቆብ እናት ማርያም ሰሎሜም ሆነው፥ የኢየሱስን አስከሬን ለመቀባት ከመልካም ቅመም የተዘጋጀ ሽቶ ገዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቶ ገዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ። |
ከዚያም ዮሴፍ የአባቱ የእስራኤል ሬሳ እንዳይፈርስ ባለመድኀኒት የሆኑ አገልጋዮቹ በመድኀኒት እንዲቀቡት አዘዘ። ባለመድኀኒቶቹም እንዳይፈርስ ሬሳውን በመድኀኒት ቀቡት።
በዳዊት ከተማ ከዐለት አስፈልፍሎ ለራሱ ባሠራውም መቃብር ቀበሩት። በቅመማ ቅመምና በልዩ ልዩ ጣፋጭ ሽቱዎች በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፤ ስለ ክብሩም ትልቅ እሳት አነደዱ።
እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ የተሠራ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፣ ብልቃጡንም ሰብራ ሽቱውን በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
በዚህ ጊዜ ሴቶች ከሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፣ የታናሹ ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፣ እንዲሁም ሰሎሜ ነበሩ፤
ዕለቱ ለሰንበት መዘጋጃ ቀን ነበር። አይሁድ፣ የተሰቀሉት ሰዎች ሬሳ በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይውል ስለ ፈለጉና ያም የተለየ ሰንበት ስለ ነበር፣ የተሰቀሉት ሰዎች ጭናቸው ተሰብሮ በድናቸው እንዲወርድ ጲላጦስን ለመኑት።