ማርቆስ 13:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜም የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ግርማ በደመና ሲመጣ ያዩታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በታላቅ ኋይልና ግርማ በደመና ሲመጣ ያዩታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ የሰው ልጅ በታላቅ ኀይልና ክብር በደመና ሲመጣ ይታያል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኀይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። |
“በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤
በዚህ ዘማዊና ኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፣ የሰው ልጅም በአባቱ ግርማ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋራ ሲመጣ ያፍርበታል።”
ቀጥሎም፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መካከል የእግዚአብሔር መንግሥት በኀይል ስትመጣ እስከሚያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ” አላቸው።
እንዲህም አሏቸው፤ “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፤ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ዘንድ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፣ ልክ ወደ ሰማይ ሲወጣ እንዳያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመለሳል።”
ጌታ ራሱ በታላቅ ትእዛዝ፣ በመላእክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር የመለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳልና። በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ።
ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ መምጣቱ የነገርናችሁ የርሱን ግርማ በዐይናችን አይተን እንጂ፣ በሰዎች ጥበብ የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም፤
“እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሳይቀሩ፣ ዐይን ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ።” አዎ! ይህ ሁሉ ይሆናል። አሜን።