ማርቆስ 12:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እንዲህ እያለ በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ ዙሪያውን ዐጠረ፤ ለመጭመቂያው ጕድጓድ ቈፈረ፤ የመጠበቂያም ማማ ሠራለት፤ ለገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም እንዲህ እያለ በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ ዙሪያውን ዐጠረ፤ ለመጭመቂያው ጉድጓድ ቆፈረ፤ የመጠበቂያም ማማ ሠራለት፤ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን በምሳሌ እንዲህ ሲል ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ዙሪያውንም ዐጠረ፤ የወይን መጭመቂያ የሚሆን ጒድጓድ ቆፍሮ አበጀ፤ ለወይኑ ጥበቃ የሚያገለግል ከፍተኛ የግንብ ማማ ሠራ፤ ከዚህም በኋላ የአትክልቱን ቦታ ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ቅጥርም ቀጠረለት፤ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፥ ቅጥርም ቀጠረለት፥ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። |
እኔ፣ እንደ ምርጥ የወይን ተክል፣ ጤናማና አስተማማኝ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ ታዲያ ብልሹ የዱር ወይን ተክል ሆነሽ፣ እንዴት ተለወጥሽብኝ?
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ምን ይመስላችኋል? ሁለት ወንዶች ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበረ፤ ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ፣ ‘ልጄ ሆይ፤ ዛሬ ወደ ወይኑ ቦታ ሄደህ ሥራ’ አለው።
“ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ አንድ የዕርሻ ባለቤት የወይን ተክል ተከለ፤ በዙሪያውም ዐጥር ዐጠረ፤ ለወይኑ መጭመቂያ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ለጥበቃ የሚሆን ማማ ሠራ፤ ከዚያም ዕርሻውን ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
ስለዚህ ለኢየሱስ፣ “አናውቅም” ብለው መለሱለት። ኢየሱስም፣ “እንግዲያውስ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
እርሱም እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ምስጢር ማወቅ ለእናንተ ተሰጥቷል፤ ለሌሎች ግን በምሳሌ እናገራለሁ፤ ይኸውም፣ “ ‘እያዩ ልብ እንዳይሉ፣ እየሰሙም እንዳያስተውሉ ነው።’
እርሱም በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋራ በምድረ በዳ በሕዝቡ ጉባኤ መካከል ነበር፤ የሕይወትንም ቃል ወደ እኛ ለማስተላለፍ ተቀበለ።