ማርቆስ 11:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት በመንገድ ሲያልፉ፣ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱ ጠዋት በመንገድ ሲያልፉ፥ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ማለዳ በመንገድ ሲያልፉ የበለሲቱ ዛፍ ከነስርዋ ደርቃ አዩአት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት። |
ተተክለው ምንም ያህል ሳይቈዩ፣ ተዘርተው ምንም ያህል ሳይሰነብቱ፣ ገና ሥር መስደድ ሳይጀምሩ አነፈሰባቸው፤ እነርሱም ደረቁ፤ ዐውሎ ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ወሰዳቸው።
እነዚህ ሰዎች በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ያለ አንዳች ኀፍረት ከእናንተ ጋራ ቀርበው የሚበሉ ነውረኞች ናቸው፤ ደግሞም ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው፤ እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው ከሥራቸው ተነቅለው ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።