ማርቆስ 11:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት!” “ሆሳዕና በአርያም!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት! ሆሣዕና በአርአያም!” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሳዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። |
የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ከልጆቹም በአብርሃም፣ በይሥሐቅና በያዕቆብ ዘር ላይ ገዥ እንዲሆኑ አልመርጥም፤ ይህንም የምለው ምርኳቸውን ስለምመልስና ስለምራራላቸው ነው።’ ”
ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በመጨረሻውም ዘመን በመንቀጥቀጥ ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።
ቀድሞት የሚሄደውና ይከተለው የነበረው ሕዝብም እንዲህ እያለ ይጮኽ ነበር፤ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ!” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!” “ሆሳዕና በአርያም!”