የእግዚአብሔር ሰው የኤልሳዕ አገልጋይ ግያዝ፣ “ጌታዬ፤ ይህ ሶርያዊ ንዕማን ያመጣውን አለመቀበሉ አይደል፤ ሕያው እግዚአብሔርን! ተከትዬ ሄጄ ከርሱ አንድ ነገር ማግኘት አለብኝ” ብሎ ዐሰበ።
ሉቃስ 7:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋበዘውም ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፣ የነካችው ሴት ማን እንደ ሆነች፣ ደግሞም ምን ዐይነት ሰው እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና” ብሎ በልቡ ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና፤” ሲል በልቡ አሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሳ የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፥ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነችና ምን ዐይነት ኃጢአተኛ እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤” ሲል በልቡ አሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። |
የእግዚአብሔር ሰው የኤልሳዕ አገልጋይ ግያዝ፣ “ጌታዬ፤ ይህ ሶርያዊ ንዕማን ያመጣውን አለመቀበሉ አይደል፤ ሕያው እግዚአብሔርን! ተከትዬ ሄጄ ከርሱ አንድ ነገር ማግኘት አለብኝ” ብሎ ዐሰበ።
‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤ አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ!’ የሚሉ ናቸው። እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።
እንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ ደግሞም በልባችሁ፣ ‘አብርሃም አባት አለን’ ማለትን አትጀምሩ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።
በዚያ ከተማ የምትኖር አንዲት ኀጢአተኛ ሴት፣ ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት በማእድ መቀመጡን በሰማች ጊዜ፣ አንድ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ሽቱ ይዛ መጣች።