ሉቃስ 7:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ ግን ትክክለኛ መሆኗ በልጆቿ ሁሉ ዘንድ ተረጋገጠ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የጥበብ መጽደቅ በልጆችዋ ሁሉ ተረጋገጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበብ ትክክለኛነት በልጆችዋ ይረጋገጣል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብም ከልጆችዋ ሁሉ ጸደቀች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥበብም ለልጆዋ ሁሉ ጸደቀች። |
ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።
የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም፣ ‘በልቶ የማይጠግብ፣ ጠጪ እንዲሁም የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ አሉት። ጥበብ ትክክለኛ መሆኗ ግን በሥራዋ ተረጋገጠ።”