ሉቃስ 6:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ለካህናት ብቻ የተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ ወስዶ በላ፤ ዐብረውት ለነበሩትም ሰጣቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዴት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር ለመብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን ኅብስት ወስዶ እንዴት እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ደግሞ እንዴት እንደሰጣቸው ይገልጥ የለምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከካህናት በቀር ለሌሎች መብላት ያልተፈቀደውን የተቀደሰ የመባ ኅብስት አንሥቶ በላ፤ ከእርሱ ጋር ለነበሩትም ሰዎች ሰጣቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንደ ገባ፥ ከካህናቱም ብቻ በቀር ሊበሉት የማይገባውን የመሥዋዕቱን ኅብስት ወስዶ እንደ በላ፥ አብረውት ለነበሩትም እንደ ሰጣቸው አላነበባችሁምን? |
ስለዚህ ካህኑ የተቀደሰውን እንጀራ ለዳዊት ሰጠው፤ ከእግዚአብሔር ፊት ተነሥቶ በትኵስ እንጀራ ከተተካው ከገጸ ኅብስቱ በቀር በዚያ ሌላ እንጀራ አልነበረምና።