“አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ ወይም ማንኛውንም እንስሳ በጎረቤቱ ዘንድ በዐደራ አስቀምጦ ሳለ እንስሳው ቢሞት ወይም ጕዳት ቢደርስበት ወይም ሰው ሳያይ ተነድቶ ቢወሰድ፣
ሉቃስ 6:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፈሪሳውያን መካከል አንዳንዶቹ ግን፣ “በሰንበት ቀን ያልተፈቀደውን ለምን ታደርጋላችሁ?” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንዶች ግን እንዲህ አሉ፦ “በሰንበት ቀን ያልተፈቀደውን ስለምን ታደርጋላችሁ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ ደቀ መዛሙርቱን “በሰንበት ቀን ሊደረግ የማይገባውን ነገር ስለምን ታደርጋላችሁ?” አሉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሪሳውያንም፥ “በሰንበት ሊደረግ የማይገባውን ለምን ታደርጋላችሁ?” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈሪሳውያን ግን አንዳንዶቹ፦ በሰንበት ሊያደርግ ያልተፈቀደውን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? አሉአቸው። |
“አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ ወይም ማንኛውንም እንስሳ በጎረቤቱ ዘንድ በዐደራ አስቀምጦ ሳለ እንስሳው ቢሞት ወይም ጕዳት ቢደርስበት ወይም ሰው ሳያይ ተነድቶ ቢወሰድ፣
ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን ማንም ቢሠራ በሞት መቀጣት አለበት።
ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የሰንበት ዕረፍት፣ የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ በዕለቱ ማንኛውንም ዐይነት ሥራ የሚሠራ ቢኖር ሞት ይገባዋል።
“እግሮችህ ሰንበትን እንዳይሽሩ ብታሳርፍ፣ በተቀደሰው ቀኔ የልብህን ባታደርግ፣ ሰንበትን ደስታ፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቀን የተከበረ ብለህ ብትጠራው፣ በገዛ መንገድህ ከመሄድ፣ እንደ ፈቃድህ ከማድረግና ከከንቱ ንግግር ብትቈጠብ፣
እነርሱም፣ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አብዛኛውን ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተዎቹ ግን ይበላሉ፤ ይጠጣሉ” አሉት።