ሉቃስ 3:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ ሕዝቡም እንደ መሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፦ የኤሊ ልጅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም አገልግሎቱን ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር፤ ይታመን እንደነበረው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ የኤሊ ልጅ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ የማስተማር ሥራውን ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያኽል ሆኖት ነበር፤ ለሕዝቡ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ ይመስላቸው ነበር፤ ይኸውም ዮሴፍ የዔሊ ልጅ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌታችን ኢየሱስም ዕድሜዉ ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ የዮሴፍ ልጅም ይመስላቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ የኤሊ ልጅ፥ |
ይህ ዐናጺው አይደለምን? የማርያም ልጅ፣ የያዕቆብ፣ የዮሴፍ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚሁ እኛው ዘንድ አይደሉምን?” ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት።
ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፣ “ሙሴ በሕግ መጻሕፍት፣ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስን አግኝተነዋል” አለው።