ከዚህም በላይ ይህች ከተማ ከተሠራች፣ ቅጥሮቿም እንደ ገና ከተገነቡ፣ ቀረጥና እጅ መንሻ ወይም ግብር እንደማይከፍሉ፣ የቤተ መንግሥቱም ገቢ እንደሚቀንስ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን።
ሉቃስ 20:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቄሣር ግብር እንድንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስቲ ንገረን! በሕጋችን መሠረት ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር መክፈል ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቄሣር ግብር መስጠት ይገባል? ወይስ አይገባም?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቄሣር ግብር ልንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም? አሉት። |
ከዚህም በላይ ይህች ከተማ ከተሠራች፣ ቅጥሮቿም እንደ ገና ከተገነቡ፣ ቀረጥና እጅ መንሻ ወይም ግብር እንደማይከፍሉ፣ የቤተ መንግሥቱም ገቢ እንደሚቀንስ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን።
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በደላችን ታላቅ ነው። ከኀጢአታችንም የተነሣ፣ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ እኛም ሆንን፣ ነገሥታቶቻችንና ካህናቶቻችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀን ለሰይፍ፣ ለምርኮ፣ ለብዝበዛና ለውርደት ተዳርገናል።
ከኀጢአታችን የተነሣ የተትረፈረፈው መከር ሲሳይ የሆነው በላያችን ላስቀመጥሃቸው ነገሥታት ነው፤ እነርሱም ደስ እንዳሰኛቸው በሰውነታችንና በቀንድ ከብቶቻችን ላይ ያዝዛሉ። እኛም በታላቅ ጭንቀት ውስጥ እንገኛለን።
እርሱም፣ “ይከፍላል እንጂ” አላቸው። ጴጥሮስ ወደ ቤት እንደ ገባ ኢየሱስ በቅድሚያ፣ “ስምዖን፤ የምድር ነገሥታት ግብር ወይም ቀረጥ የሚቀበሉት ከራሳቸው ልጆች ወይስ ከሌሎች ይመስልሃል?” አለው።
ሰላዮቹም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ ትክክለኛውን ነገር እንደምትናገርና እንደምታስተምር እንዲሁም የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምርና ለማንም እንደማታደላ እናውቃለን።
እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክል፣ ደግሞም፣ ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’ ሲል አገኘነው።”
ከርሱም በኋላ፣ በሕዝብ ቈጠራው ወቅት ገሊላዊው ይሁዳ ተነሥቶ ብዙ ሕዝብ አሸፈተ፤ ተከታይም አግኝቶ ነበር፤ እርሱም ጠፋ፤ ተከታዮቹም ተበተኑ።
አምላክህ እግዚአብሔር የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ታነግሣለህ፤ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ፣ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ።