Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 20:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሰላዮቹም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ ትክክለኛውን ነገር እንደምትናገርና እንደምታስተምር እንዲሁም የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምርና ለማንም እንደማታደላ እናውቃለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት “መምህር ሆይ! እውነትን እንደምትናገርና እንደምታስተምር በሰው ፊትም እንደማታደላ እናውቃለን፤ ይልቁንም በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ ታስተምራለህ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሰላዮቹም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ “መምህር ሆይ! አንተ የምትናገረውና የምታስተምረው እውነት መሆኑን እናውቃለን፤ የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት ታስተምራለህ እንጂ ለማንም አታዳላም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ አንተ እው​ነት እን​ደ​ም​ት​ና​ገ​ርና እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ፊት አይ​ተ​ህም እን​ደ​ማ​ታ​ዳላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ገድ በቀ​ጥታ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር እና​ው​ቃ​ለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ጠይቀውም፦ መምህር ሆይ፥ እውነትን እንድትናገርና እንድታስተምር ለሰው ፊትም እንዳታደላ እናውቃለን፥ በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ ታስተምራለህ እንጂ፤

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 20:21
16 Referencias Cruzadas  

ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ወገኖች ጋራ ወደ እርሱ ልከው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛና የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት የምታስተምር እንደ ሆንህ፣ ለማንም ሳታደላ ሁሉን እኩል እንደምትመለከት እናውቃለን፤


አሁን እኔ ተቀባይነት ለማግኘት የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሠኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሠኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁ ነበር።


እኛ እኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።


በሌሊትም ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ “ረቢ፤ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ከሆነ ሰው በቀር አንተ የምታደርጋቸውን ታምራዊ ምልክቶች ማንም ሊያደርግ ስለማይችል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንህ እናውቃለን” አለው።


እነርሱም መጥተው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛ ሰው መሆንህን፣ ለማንም ሳታደላ ሁሉንም እኩል እንደምትመለከት እናውቃለን፤ ይልቁንስ የእግዚአብሔርን መንገድ ብቻ በእውነት ታስተምራለህ፤ ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?


አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው፤ በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው፤ ይሁን እንጂ የተመዘዘ ሰይፍ ነው።


እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ።


ሁሉም የእጁ ሥራ ስለ ሆኑ፣ እርሱ ለገዦች አያደላም፤ ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።


አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ማጣመም፣ አድልዎ ማድረግና መማለጃ መቀበል ስለሌለ ተጠንቅቃችሁ ፍረዱ።”


ዋነኛ መስለው ስለሚታዩት ሰዎች ማንነት እኔን አይገደኝም፤ እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፤ እነዚህም ሰዎች ለመልእክቴ የጨመሩልኝ ነገር የለም።


ኢየሱስን አሳልፈው ለገዢው ኀይልና ሥልጣን ለመስጠት፣ ከአፉ በሚወጣ ቃል ለማጥመድ ይከታተሉት ነበር፤ ስለዚህም ጻድቃን መስለው የሚቀርቡ ሰላዮችን ላኩበት።


ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios