La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 2:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕፃኑም እያደገ፣ እየጠነከረም ሄደ፤ በጥበብ ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በርሱ ላይ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕፃኑም አደገ ጠነከረም፤ ጥበብም ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ ሄደ፤ በጥበብም የተሞላ ሆነ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ ከእርሱ ጋር ነበረ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 2:40
17 Referencias Cruzadas  

አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤ በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።


አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ፤ ከንፈሮችህም የጸጋ ቃል ያፈልቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል።


ሕፃኑም እያደገ፣ በመንፈስም እየጠነከረ ሄደ፤ ለእስራኤልም ሕዝብ በይፋ እስከ ታየበት ቀን ድረስ በበረሓ ኖረ።


የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይደነቁ ነበር።


ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አደገ።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን።


ሐዋርያትም ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በታላቅ ኀይል መመስከራቸውን ቀጠሉ፤ በሁላቸውም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበር።


በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ።


እንግዲህ ልጄ ሆይ፤ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።


ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሳምሶን ብላ ጠራችው። ልጁ አደገ፤ እግዚአብሔርም ባረከው፤


ብላቴናው ሳሙኤል ግን ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር።


እግዚአብሔርም ሐናን ዐሰባት፤ ፀነሰችም፤ ሦስት ወንዶች፣ ሁለት ሴቶች ልጆችም ወለደች። ብላቴናውም ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት አደገ።


ብላቴናውም ሳሙኤል በአካልና በሞገስ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት እያደገ ሄደ።


ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ስለ ነበረ፣ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር።