እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው።
ሉቃስ 19:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያንም ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፤ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው እንጂ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕዝቡም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ “መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው፤” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቡ መካከል የነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን “መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ዝም አሰኛቸው!” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈሪሳውያንም በሕዝቡ መካከል፥ “መምህር ሆይ፥ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው” ያሉት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕዝብም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ፦ መምህር ሆይ፥ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው።
“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገቡ በሩን ስለምትዘጉባቸው እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ መግባት የሚፈልጉትንም አታስገቡም። [