የተላኩትም ሄደው ልክ እንደ ነገራቸው ሆኖ አገኙት።
የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው ሆኖ አገኙት።
የተላኩትም ሄደው ሁሉም ነገር ልክ ኢየሱስ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት።
የተላኩትም ሄደው እንደ አላቸው አገኙ።
የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ።
ማንም፣ ‘ለምን ትፈቱታላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል’ በሉት።”
ባለቤቶቹም ውርንጫውን ሲፈቱ አይተው፣ “ውርንጫውን ለምን ትፈታላችሁ?” አሏቸው።
እነርሱም ሄደው ልክ ኢየሱስ እንደ ነገራቸው ሆኖ አገኙት፤ ፋሲካንም በዚያ አዘጋጁ።