ሉቃስ 19:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታውም፣ ‘አንተ ታማኝ ባሪያ፣ መልካም አድርገሃል፤ በትንሽ ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ፥ በጥቂት ነገር የታመንህ ስለ ሆንክ በዐሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ፤’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታውም ‘አንተ መልካም አገልጋይ! ደግ አደረግህ፤ በትንሽ ነገር ስለ ታመንህ እኔ ደግሞ በዐሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለሆንህ በብዙ ላይ እሾምሃለሁ፤ በዐሥሩ ከተሞች ላይ ተሾም አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው። |
“ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ ባሪያ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።
ይኸውም በመንግሥቴ ከማእዴ እንድትበሉና እንድትጠጡ፣ ደግሞም በዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ እንድትፈርዱ ነው።”
ዳሩ ግን አንድ ሰው ይሁዲ የሚሆነው በውስጣዊ ማንነቱ ይሁዲ ሆኖ ሲገኝ ነው። ግዝረትም ግዝረት የሚሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ በመንፈስ የልብ ግዝረት ሲኖር ነው። እንዲህ ያለው ሰው ምስጋናው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ የደረሱት፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ፣ እውነተኛ መሆኑ እንዲረጋገጥና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ክብርንና ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።
“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ቤትህና የአባትህ ቤት በፊቴ ለዘላለም ያገለግሉኝ ዘንድ ተስፋ ሰጥቼ ነበር፤’ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ከእንግዲህ አላደርገውም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ፤ የሚንቁኝም ፈጽሞ ይናቃሉ።