ሉቃስ 19:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የመጀመሪያው አገልጋይ ቀርቦ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ የሰጠኸኝ ምናን ዐሥር ምናን ትርፍ አስገኝቷል’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጀመሪያውም ደርሶ ‘ጌታ ሆይ! ምናንህ ዐሥር ምናን አተረፈ፤’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው አገልጋይ ቀርቦ፦ ‘ጌታ ሆይ! የሰጠኸኝ አንድ ምናን እነሆ፥ ዐሥር ምናን አትርፎአል’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደኛውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምናንህ ዐሥር ነበር፤ እነሆ ዐሥር ምናን አትርፌአለሁ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛውም ደርሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው። |
“ይሁን እንጂ ይህ መስፍን ንጉሥ ሆኖ ወደ አገሩ ተመለሰ፤ እነዚያ ባሮችም እርሱ በሰጣቸው ገንዘብ ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ለማወቅ አስጠራቸው።
“ጌታውም፣ ‘አንተ ታማኝ ባሪያ፣ መልካም አድርገሃል፤ በትንሽ ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ እንዲያውም ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ዳሩ ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋራ ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።