እረኛ ከመንጋው ጋራ ሳለ፣ የተበተኑበትን በጎች እንደሚፈልግ ሁሉ፣ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ። በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።
ሉቃስ 19:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው። |
እረኛ ከመንጋው ጋራ ሳለ፣ የተበተኑበትን በጎች እንደሚፈልግ ሁሉ፣ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ። በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።
የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትንም እመልሳለሁ። የተጐዱትን እጠግናለሁ፤ የደከሙትንም አበረታለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውን ግን አጠፋለሁ። መንጋውን በፍትሕ እጠብቃለሁ።
“ከእነዚህ ከታናናሾች መካከል አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ እላችኋለሁና፤ በሰማይ ያሉት መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉ፤ [
“ወይም ዐሥር የብር ሳንቲሞች ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ ቢጠፋባት፣ እስክታገኘው ድረስ መብራት አብርታ፣ ቤቷን ጠርጋ፣ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?