የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም፣ ‘በልቶ የማይጠግብ፣ ጠጪ እንዲሁም የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ አሉት። ጥበብ ትክክለኛ መሆኗ ግን በሥራዋ ተረጋገጠ።”
ሉቃስ 15:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም፣ “ይህ ሰው ኀጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋራ ይበላል” እያሉ አጕረመረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሪሳውያንና ጻፎችም “ይህስ ኀጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር ይበላል፤” ብለው እርስ በርሳቸው አጉረመረሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን ይህን አይተው፦ “ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር አብሮ ይበላል” እያሉ በኢየሱስ ላይ አጒረመረሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “ይህስ ኀጢኣተኞችን ይቀበላል፤ አብሮአቸውም ይበላል” ብለው አንጐራጐሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሪሳውያንና ጻፎችም፦ ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ። |
የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም፣ ‘በልቶ የማይጠግብ፣ ጠጪ እንዲሁም የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ አሉት። ጥበብ ትክክለኛ መሆኗ ግን በሥራዋ ተረጋገጠ።”
ፈሪሳውያንና ጸሐፍታቸውም “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ‘ከኀጢአተኞች’ ጋራ የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” እያሉ በደቀ መዛሙርቱ ላይ አጕረመረሙ።
የጋበዘውም ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፣ የነካችው ሴት ማን እንደ ሆነች፣ ደግሞም ምን ዐይነት ሰው እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና” ብሎ በልቡ ዐሰበ።
አንዳንድ ሰዎች ከያዕቆብ ዘንድ ከመምጣታቸው በፊት፣ ከአሕዛብ ጋራ ይበላ ነበር፤ እነርሱ በመጡ ጊዜ ግን፣ የተገረዙትን ወገኖች ፈርቶ ከአሕዛብ ራሱን በመለየት ገሸሽ ማለት ጀመረ፤
“ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።